የX ደንቦች

የX አላማ የህብረተሰብ ንግግርን ለማገልገል ነው። ሁከት፣ ጥቃት እና ሌሎች የመሳሰሉት ባህሪያት ሰዎች እራሳቸውን እንዳይገልጹ ተስፋ ያስቆርጣቸዋል፣ እንደዚሁም አለማቀፋዊ የህብረተሰብ ንግግርን ዋጋ ያሽቆለቁላል። ደንቦቻችን ሁሉም ሰዎች በህብረተሰብ ንግግር ውስጥ በነጻነት እና በደህንነት እንዲሳተፉ ያረጋግጣሉ።
 

ደህንነት

ጠበኛ ንግግር: ማስፈራራት, ማነሳሳት, ማሞገስ, ወይም ለጥቃት ወይም ለመጉዳት ፍላጎትን መግለፅ አይችሉም. የበለጠ ይማሩ

ጠበኛ እና የጥላቻ አካላት፡ :ከጥቃት እና ከጥላቻ አካላት ጋር መቆራኘት ወይም ማስተዋወቅ አይችሉም። የበለጠ ይማሩ

የህፃናት ፆታዊ ጥቃት፦ X ላይ ለሚደረግ የህፃናት ፆታዊ ጥቃት ትዕግስታችን ዜሮ ነው። የበለጠ ይማሩ

ማጎሳቆል/ትንኮሳ፡ ተሳዳቢ ይዘትን ማጋራት፣ በአንድ ሰው ላይ ያነጣጠረ ትንኮሳ ውስጥ መሳተፍ ወይም ሌሎች ሰዎች እንዲያደርጉ ማነሳሳት አይችሉም። የበለጠ ይማሩ

በጥላቻ የተሞላ ባህሪ፡ በሌሎች ላይ ሁከትን፣ ዛቻን፣ ወይንም ሌሎች ሰዎችን በዘራቸው፣ በማንነታቸው፣ በትውልድ ቦታቸው፣ በደረጃቸው፣ በጾታ ዝንባሌያቸው፣ በጾታቸው፣ በጾታ ማንነታቸው፣ በሃይማኖት አመለካከታቸው፣ በእድሜያቸው፣ በአካል ጉዳተኝነታቸው ወይንም በከባድ በሽታቸው ምክንያት ትንኮሳ እንዲደረግ ማስተዋወቅ/ማነሳሳት ወይም በቀጥታ ጥቃት ማድረስ ወይም ማስፈራራት አይችሉም። የበለጠ ይማሩ። 

የሁከት ጥቃት ወንጀለኞች፦ በአሸባሪ፣ አዋኪ ፅንፈኝነት ወይንም የጅምላ የሁከት ጥቃት ወንጀለኞች የሚተዳደሩ ማንኛውንም መለያዎች እንሰርዛለን፣ እንደዚሁም ማኒፌስቶዎችን ወይንም ሌሎች በወንጀለኞች የተዘጋጁ ይዘቶችን የያዙ የX ልጥፎችን እንሰርዛለን። የበለጠ ይማሩ። 

ራስን ማጥፋት፡ ራስን ማጥፋትን ወይም ራስን መጉዳትን ማስተዋወቅ ወይም ማበረታታት አይችሉም። የበለጠ ይማሩ

ስሜታዊ የሚያደርጉ ይዘቶች፡ንድፋዊ ሁከት እና የአዋቂ ይዘቶችን ጨምሮ፣ በከፍተኛ ሁኔታ አዋኪ የሆኑ ልጥፎችን መለጠፍ ወይንም ሁከት ወይም የአዋቂ ይዘትን በቀጥታ ስርጭት ወይንም ፕሮፋይል ላይ ወይንም የራስጌ ምስል ላይ በመለጠፍ ማጋራት አይችሉም። እንደዚሁም በሚዲያ ፆታዊ ሁከት እና/ወይንም ጥቃትን ማስፋፋት የተከለከለ ነው። የበለጠ ይማሩ። 

ህገወጥ ወይም የተወሰኑ ቁጥጥር የሚደረግባቸው እቃዎች ወይም አገልግሎቶች፡ አገልግሎታችንን ለማንኛውም ህገወጥ ዓላማ ወይም ህገወጥ ተግባራትን ለማራመድ መጠቀም አይችሉም። ይሄም በህገወጥ እቃዎች እና አገልግሎቶች ላይ እንደዚሁም ቁጥጥር የሚደረግባቸው እቃዎች እና አገልግሎቶችን መሸጥ፣ መግዛት ወይንም ግብይት ማመቻቸትን የሚያጠቃልል ይሆናል። የበለጠ ይማሩ

ግላዊነት

 

የግል መረጃዎች፦ የሌሎች ሰዎች የግል መረጃዎችን (እንደ የቤት ስልክ ቁጥር እና አድራሻ አይነቶች) ያለ እነሱ ትዕዛዝ እና ፈቃድ መለጠፍም ሆነ ማተም አይችሉም። እንደዚሁም የሌሎችን የግል መረጃ ለማውጣት ማስፈራራት እና ሌሎችም ይህንን እንዲያደርጉ መገፋፋትን እንከለክላለን። የበለጠ ይማሩ

ያለ ፈቃድ የእርቃን ይዘትን ማሰራጨት፡ ያለፈቃዳቸው የተሰራ ወይም የተሰራጨ የአንድ ሰው የእርቃን ፎቶዎችን ወይም ቪዲዮዎችን መለጠፍ ወይም ማጋራት አይችሉም። የበለጠ ይማሩ

የመለያ መጠቃት፦ የመግቢያ ማስረጃዎችን፣ የይለፍ ቃሎችን፣ ቶክኖችን፣ ቁልፎችን፣ ኩኪዎችን ወይንም ለመግባት የሚረዱ ሌሎች ውሂቦችን መጠቀም ወይም ከእርስዎ (ወይንም በX ቡድኖች ፈቃድ ወይንም OAuth ፈቃድ ወይንም በተመሳሳይ መንገድ በቀጥታ እንዲያደርጉ የታዘዙት) ውጪ የሆነን የX መለያ ባህሪያትን ወይም የግል መረጃን መጠቀም፣ ማከል፣ ማጥፋት ወይንም ማሻሻል ወይም እነዚህን ለማድረግ መሞከር አይችሉም። የበለጠ ይማሩ

ትክክለኛነት


ፕላትፎርሙን ማዛባት እና ማጭበርበር፦
በሰውሰራሽ ማግዘፍ ወይንም መረጃን በመደበቅ ባለመ መንገድ የX አገልግሎትን መጠቀም ወይንም ሰዎች X ላይ ያላቸውን ተሞክሮ የሚቆጣጠር ወይንም የሚያበላሽ ባህርይ ላይ መሳተፍ አይችሉም። የበለጠ ይማሩ

የሲቪክ ቅንጅት፦ የX አገልግሎቶችን የምርጫ ስነስርዓቶችን ወይንም ሌሎች የሲቪክ ሂደቶችን ለማዛባት ወይንም ጣልቃ ለመግባት አላማ መጠቀም አይችሉም። ይሄም ሰዎች መቼ፣ የት ወይንም እንዴት የሲቪክ ሂደት ውስጥ መሳተፍ እንዳለባቸው ጫና የሚፈጥር ወይም የሚያሳስት ይዘትን መለጠፍ እና ለሰዎች ማጋራትን ይጨምራል። የበለጠ ይማሩ

የሚያስቱ እና የሚሸውዱ ማንነቶች ግለሰቦችን፣ ቡድኖችን ወይንም ተቋማትን ለማሳሳት ወይንም ለመሸወድ ወይንም ለማታለል እነርሱን እንደሆኑ ማስመሰል፣ ሌሎች ተጠቃሚዎች የX ተሞክሯቸውን በሚረብሽ መንገድ የውሸት ማንነትን መጠቀም አይችሉም። የበለጠ ይማሩ

ሰው ሰራሽ እና የተቀነባበረ ሚዲያ፡ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ሰው ሰራሽ ወይም የተቀነባበሩ ሚዲያዎችን በማታለል ላያካፍሉ ይችላሉ። በተጨማሪ ሰዎች እውነታውን እንዲያረጋግጡ ለመርዳት እና ተጨማሪ አውድ ለማቅረብ የተፈበረከ እና የውሸት ሚዲያን ያካተቱ የX ልጥፎችን ለይተን እናስቀምጣለን። የበለጠ ይማሩ

የቅጂ መብት እና የንግድ ምልክት: የቅጂ መብት እና የንግድ ምልክትን ጨምሮ የሌሎችን የአእምሮአዊ ንብረት መብቶችን መጣስ አይችሉም። ስለ እኛ የንግድ ምልክት መመሪያ እና የቅጂ መብት መመሪያ የበለጠ ይማሩ።

በቪዲዮ ይዘት ላይ የሶስተኛ ወገን ማስታወቂያ


እንደ ቀድሞ የሚመጣ የቪዲዮ ማስታወቂያ ወይንም የስፖንሰር ግራፊክስ ያሉ የሶስተኛ ወገን ማስታወቂያዎችን የሚያካትት ያለ እኛ ቅድመ ፈቃድ በኛ አገልግሎት ላይ ወይንም በኩል የትኛውንም የቪድዮ ይዘት ማስገባት፣ መለጠፍ ወይንም ማሳየት አይችሉም።


ማስፈጸሚያ እና ይግባኝ


እነዚህን ደንቦች ለሚተላለፉ ወይንም በብልጠት ህግ ማስከበርን ለመተላለፍ ለሚሞክሩ የሚያስከትለውን ውጤትን እንደዚሁም እንዴት ይግባኝ እንደሚጠየቅ ጨምሮ ስለ የህግ ማስከበር አካሄዳችን የበለጠ ይማሩ።

ይሄንን ጽሁፍ ያጋሩ