ስለ መለያ ደህንነት

የመለያዎን ደህንነት ለማስጠበቅ እንዲረዳ፣ የሚከተሉትን ምርጥ ተሞክሮዎች እንመክራለን

  • በሌሎች ድረ-ገጾች ላይ ዳግም የማይጠቀሙበት ጠንካራ የይለፍ ቃል ይጠቀሙ።
  • Tባለ ሁለት-መስፈርት ማረጋገጫ ይጠቀሙ።
  • አዲስ የይለፍ ቃል ማግኛ አገናኝ ወይም ኮድ ለመጠየቅ ኢሜይል እና ስልክ ቁጥር ይጠይቁ።
  • አጠራጣሪ አገናኞችን ይጠንቀቁ፣ እንዲሁም የመግቢያ መረጃዎን ከማስገባትዎ በፊት በ twitter.com ላይ መሆንዎን ያረጋግጡ።
  • የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃልዎን ለሶስተኛ ወገኖች ፣ በተለይም ተከታዮች ሊያመጡልዎ፣ ገንዘብ ሊያስገኙልዎ፣ ወይም ሊያረጋግጡልዎ ቃል ለሚገቡ አሳልፈው አይስጡ።
  • የኮምፒውተር ሶፍትዌርዎ፣ አሳሽዎን ጨምሮ፣ የቅርብ ጊዜው ማሻሻያ እንደተደረገለት እና የጸረ-ቫይረስ ሶፍትዌር እንደተጫነለት ያረጋግጡ።
  • መለያዎ ጥሰት ተፈጽሞበት እንደሆነ ይፈትሹ።

የይለፍ ቃል ጥንካሬ

ለX መለያዎ ጠንካራ እና ልዩ የይለፍ ቃል ይፍጠሩ። በተጨማሪም ከX መለያዎ ጋር ለተቆራኘው ኢሜይልዎ በተመጣጣኝ ደረጃ ጠንካራ እና ልዩ የሆነ የይለፍ ቃል መፍጠር አለብዎት።

ይኽን ያድርጉ፦

  • ያድርጉ ቢያንስ የ10 ቁምፊዎች እርዝመት ያለው የይለፍ ቃል ይፍጠሩ። ረጅም የተሻለ ነው።
  • ያድርጉ የዐብይ ሆሄ፣ የንዑስ ሆሄ፣ ቁጥር እና ምልክቶችን ድብልቅ ይጠቀሙ።
  • ያድርጉ ለእያንዳንዱ ለሚጎበኙት ድር -ገጽ የተለያየ የይለፍ ቃል ይጠቀሙ።
  • ያድርጉ የይለፍ ቃልዎን ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ያስቀምጡ። ሁሉንም የመግቢያ መረጃ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለማስቀመጥ የይለፍ ቃል አስተዳዳሪ ሶፍትዌር መጠቀምን ያስቡበት።

ይኽን አያድርጉ፦

  • አያድርጉ የይለፍ ቃልዎ ውስጥ የግል መረጃ፣ ለምሳሌ ስልክ ቁጥሮች፣ የልደት ቀናት፣ ወዘተ አይጠቀሙ።
  • አያድርጉ እንደ “የይለፍ ቃል” እና “እወድሻለሁ” ወዘተ የመሳሰሉ የተለመዱ የመዝገበ ቃላት ቃላትን አይጠቀሙ።
  • አያድርጉ እንደ ”abcd1234”፣ ወይም እንደ “qwerty” የመሳሰሉ የቁልፍ ሰሌዳ ቅደም ተከተሎችን አይጠቀሙ።
  • አያድርጉ የይለፍ ቃላትን በበርካታ ድር-ገጾችላይ በድጋሚ አይጠቀሙ። የX መለያ የይለፍ ቃልዎ ለX ብቸኛ መሆን አለበት።

በተጨማሪም፣ የይለፍ ቃል እንደገና ማስጀመር ጥበቃን በእርስዎ መለያ ቅንብሮች ውስጥ መምረጥ ይችላሉ። ይህ ሳጥን ላይ ምልክት የሚያደርጉ ከሆነ፣ ምናልባት የይለፍ ቃልዎን ቢረሱ የይለፍ ቃል እንደገና ማስጀመሪያ አገናኝ ወይም የማረጋገጫ ኮድ እንዲላክልዎ ኢሜይል አድራሻዎን ወይም ስልክ ቁጥርዎን፣ ወይም ሁለቱም ከX መለያዎ ጋር የተገናኙ ከሆነ መጀመሪያ ኢሜይል አድራሻዎን ከዚያም ስልክ ቁጥርዎን እንዲያስገቡ ሊጠየቁ ይችላሉ። 

የይለፍ ቃል እንደገና ማስጀመሪያ ቅንብሮችን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ
  1. ወደ ዋናው ምናሌዎ ይሂዱ
  2. ቅንብሮችን እና ግላዊነትን መታ ያድርጉ
  3. መለያን መታ ያድርጉ
  4. ደህንነትን መታ ያድርጉ
  5. የይለፍ ቃል እንደገና ማስጀመሪያ ጥበቃን ያብሩ
  1. ወደ መተግበሪያ ቅንብሮችዎ ያስሱ
  2. መለያን መታ ያድርጉ
  3. ደህንነትን መታ ያድርጉ
  4. የይለፍ ቃል እንደገና ማስጀመሪያ ጥበቃን ይቀያይሩ
ባለ ሁለት-መስፈርት ማረጋገጫን ይጠቀሙ

ባለ ሁለት መስፈርት ማረጋገጫ ለመለያዎ ተጨማሪ የደህንነት ደርብ ነው። በይለፍ ቃል ብቻ ከመተማመን፣ ባለ ሁለት መስፈርት ማረጋገጫ፣ የX መለያዎ ዘንድ የሚደርሱት እርስዎ እና እርስዎ ብቻ መሆንዎን ለማረጋገጥ ሁለተኛ ማረጋገጫ ይጨምራል። ወደ ሁለቱም የይለፍ ቃልዎ እና ሞባይል ስልክዎ (ወይም የደህንነት ቁልፍ) መዳረሻ ያለው ሰው ብቻ ወደ መለያዎ መግባት ይችላል።

የበለጠ ለመረዳት ስለ ባለ-ሁለት መስፈርት ማረጋገጫ ጽሁፋችንን ያንብቡ።

twitter.com ላይ ያሉ መሆንዎን ያረጋግጡ

ማስገር የሚባለው አንድ ሰው የX መለያዎን የኢሜይል አድራሻዎን ወይም ስልክ ቁጥርዎን እና የይለፍ ቃልዎን እርስዎን በማታለል ማግኘት ሲችል ነው፤ ይኽን የሚያደርጉት ከእርስዎ መለያ ሆነው አይፈለጌ ለመላክ ነው። ብዙዎን ጊዜ ሊያታልሉዎ የሚሞክሩት ወደ የሐስት መግቢያ ገጽ የሚወስድ አገናኝ በመላክ ነው። የX የይለፍ ቃል እንዲያስገቡ በሚጠየቁ ጊዜ፣ በ twitter.com ላይ ያሉ መሆንዎን ለማረጋገጥ በአሳሽዎ የአድራሻ አሞሌ ላይ ዩአርኤሉን ይመልከቱ። በተጨማሪም፣ ያልተለመደ የሚመስል አገናኝ የያዘ የቀጥታ መልዕክት በሚቀበሉ ጊዜ (ከጓደኛም ቢሆን)፤ አገናኙን እንዳይከፍቱት እንመክራለን።

አስጋሪ ድር ጣቢያዎች ልክ የXን የመግቢያ ገጽ ይመስላሉ፣ ነገር ግን በተጨባጭX ያልሆኑ ገጾች ይሆናሉ። የX ጎራዎች ሁልጊዜ እንደ መሰረት ጎራቸው https://twitter.com/ ይኖራቸዋል። አንዳንድ የX የመግቢያ ገጾች ምሳሌዎች እነሆ፦

ስለ አንድ የመግቢያ ገጽ እርግጠኛ ካልሆኑ፣ በቀጥታ ወደ twitter.com ይሂዱ እና የመግቢያ መረጃዎን እዚያ ያስገቡ። ከዚህ ቀደም የማስገር ጥቃት ደርሶብዎ እንደሆነ ካሰቡ፣ የይለፍ ቃልዎን በተቻለዎ ፍጥነት ይቀይሩ እና ለተጨማሪ መመሪያ የተጠቃ መለያ ጽሁፋችንን ያንብቡ። 

በኢሜይል ስለማስገር የሐሰት የX ኢሜይሎች ያንብቡ። 

የይለፍ ቃልዎን ለመጠየቅ ብለን አናነጋግርዎትም

X የይለፍ ቃልዎን እንዲሰጡ በኢሜይል፣ በቀጥታ መልዕክት፣ ወይም በምላሽ በፍጹም አይጠይቅም።

አንድን ነገር እንዲያወርዱ ወይም የtwitter ወዳልሆነ ድር ጣቢያ በመለያ እንዲገቡ በፍጹም አንጠይቅዎትም። ከእኛ እንደሆነ ተደርጎ ከሚላክልዎ ኢሜይል አባሪዎችን አይክፈቱ ወይም ምንም ሶፍትዌር አይጫኑ፤ ከእኛ አይደለም።

መለያዎ የማስገር ጥቃት እንደደረሰበት ወይም እንደተጠቃ ካሰቡ፣ አጥቂው መለያዎን ያላግባብ እንዳይጠቀምበት ለመከላከል የይለፍ ቃልዎን እንደእገና ልናስጀምር እንችላለን። ይህ ከሆነ፣ የ twitter.com የይለፍ ቃል እንደገና ማስጀመሪያ አገናኝ በኢሜይል እንልክልዎታለን።

የይለፍ ቃልዎን ከረሱ፣ በዚህ አገናኝ መስመር አማካኝነት እንደገና ማስጀመር ይችላሉ።

 

አዲስ እና አጠራጣሪ በመለያ የመግባት ማንቂያዎች

አጠራጣሪ በመለያ መግባትን ወይም ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ መሳሪያ ወደ X መለያ በሚገቡ ጊዜ፣ ለመለያዎ እንደ ተጨማሪ የደህንነት ደርብ በX መተግበሪያ ውስጥ ተገፊ ማሳወቂያ ወይም ወደ ኢሜይልዎ እንልክልዎታለን። በመለያ የመግባት ማንቂያዎች የሚላኪት አዲስ መግቢያዎችን ተከትለው ብቻ ሲሆን በTwiitter ለiOS፣ X ለ Android፣ X.com፣ እና ሞባይል ድር ላይ ነው።

በእነዚህ ማንቂያዎች አማካኝነት፣ ከመሳሪያው የገባው እርስዎ ብቻ መሆንዎን ማረጋገጥ ይችላሉ። ከመሳሪያው ካልገቡ፣ የመለያዎን ደህንነት ለመጠበቅ የX የይለፍ ቃልዎን ወዲያው ከመቀየር ጀምረው በማሳወቂው ውስጥ ያሉትን ቅደም ተከተሎች መከተል አለብዎ። እባክዎ በማሳወቂያው ውስጥ የተገለጸው ቦታ X ጋርለመድረስ ከአይፒ (IP ) አድራሻው የተቀዳ ተቀራራቢ የግምት ቦታ መሆኑን እና ከአካላዊ የመገኛ ቦታዎ የተለየ ሊሆን እንደሚችል ይገንዘቡ።

ያስታውሱ፦ ወደ X መለያዎ ከincognito (ማንነት የማያሳውቅ) አሳሾች ወይም ኩኪዎች ከተሰናከሉበት አሳሽ የሚገቡ ከሆነ፤ በእያንዳንዱ ጊዜ ማንቂያ ይደርስዎታል።

የኢሜይል አድራሻ ማደስ ማንቂያዎች

ከX መለያዎ ጋር የተቆራኘው ኢሜይል በሚቀየር ጊዜ፣ ከዚህ ቀደም በመለያዎ ላይ ጥቅም ላይ ወደዋለው ኢሜይልዎ የኢሜይል ማሳወቂያ እንልካለን። መለያዎ የተጠቃ በሚሆን ጊዜ፣ እነዚህ ማንቂያዎች መለያዎን መልሰው መቆጣጠር የሚያስችሉዎ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ይረዱዎታል።
 

በX ላይ ያሉ አገናኝ መስመሮችን መገምገም

በርካታ የX ተጠቃሚዎች እንደ bit.ly ወይም TinyURLን የመሳሰሉ የዩአርኤል ማሳጠሪያዎችን በመጠቀም በX ላይ ለማጋራት ቀላል የሆኑ አገናኞችን ይለጥፋሉ። ይሁን እንጂ፣ ዩአርኤል ማሳጠሪያዎች መነሻ ጎራውን ሊደብቁ ይችላሉ፣ ይኽም አገናኙ ወዴት እንደሚወስድ ማወቅን አዳጋች ያደርገዋል።

አዳንድን አሳሾች፣ ለምሳሌ Chrome እና Firefox፣ እርስዎ እነርሱን ጠቅ ማድረግ ሳያስፈልግዎ የተራዘሙትን ዩአርኤሎች የሚያሳዩ ነጻ ተቀጥላዎች አሏቸው።

በአጠቃላይ፣ እባክዎ በአገናኞች ላይ ጠቅ በሚያደርጉ ጊዜ ጥንቃቄ ያድርጉ። አንድን አገናኝ ጠቅ ቢያደርጉ እና እራስዎን ሳያውቁት የX መግቢያ ገጽ የሚመስል ገጽ ላይ አርፈው ቢያገኙ፣ የተጠቃሚ ስምዎን እና የይለፍ ቃልዎን አያስገቡ። ከዚያ ይልቅ፣ ወደ X.com ይሂዱ እና ከX መነሻ ገጽ በቀጥታ ይግቡ።
 

ኮምፒውተርዎን እና አሳሽዎን ወቅታዊና ከቫይረስ-ነጻ እንደሆነ ያቆዩ

አሳሽዎን እና ሥርዓተ ክወናዎን በቅርብ ጊዜዎቹ ስሪቶች እና ጥገናዎች እንደዘመኑ ያቆዩ - ጥገናዎች ብዙውን ጊዜ የሚለቀቁት የታወቁ የደህንነት ስጋቶችን ለመጠገን ነው። በተጨማሪም ኮምፒውተርዎ ቫይረሶች፣ ስፓይዌር፣ እና አድዌር መኖሩን ለመፈተሽ በየጊዜው ስካን ማድረግዎን እርግጠኛ ይሁኑ።

የሕዝብ ኮምፒውተር እየተጠቀሙ ከሆነ፣ በሚጨርሱ ጊዜ ከX ዘግተው መውጣትዎን ያረጋግጡ።

የሶስትኛ-ወገን መተግበሪያዎችን በጥንቃቄ ይምረጡ

ከX መለያ(ዎች)ዎ ጋር ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸው በውጫዊ ገንቢዎች በX መድረክ ላይ የተገነቡ በርካታ የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች አሉ። ይሁን እንጂ፣ ለሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች ወደ X መለያዎ መዳረሻ ከመስጠትዎ በፊት ጥንቃቄ ማድረግ አለብዎ።

ለሶስተኛ ወገን መተግበሪያ ወደ መለያዎ መዳረሻ ለመስጠት ከፈለጉ፣ የX OAuth ዘዴን በመጠቀም ብቻ እንዲያደርጉት እንመክራለን። OAuth ደህንነቱ የተጠበቀ ዘዴ ሲሆን የTwitteerን የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል ለሶስተኛ ወገን እንዲያጋሩ አያስገድድዎትም። እንዲሁም ለመተግበሪያ ወይም ድር ጣቢያ፣ የተጠቃሚ ስምዎን እና የይለፍ ቃልዎን እንዲሰጡ ቢጠየቁ ጥንቃቄ ማድረግ አለብዎ፣ ምክንያቱም የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች በOAuth አማካኝነት ወደ መለያዎ መዳረሻ በሚያገኙ ጊዜ የተጠቃሚ ስምዎ እና የይለፍ ቃልዎ አያስፈልጋቸውም። የተጠቃሚ ስምዎን እና የይለፍ ቃልዎን ለሌላ ሰው በሚሰጡ ጊዜ፣ የእርስዎ መለያ ሙሉ ቁጥጥር ይኖራቸዋል እንዲሁም እርስዎ እንዳይደርሱበት ማድረግ እና መለያዎ እንዲታገድ ሊያስደርጉ የሚችሉ ድርጊቶችን ሊፈጽሙበት ይችላሉ። ለሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎችን ስለ መፍቀድ እና መከልከል ይወቁ።

ወደ መለያዎ መዳረሻ ያላቸውን የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲገመግሟቸው እንመክራለን። ለማያውቋቸው ወይም እርስዎን በመሆን ትዊት የሚያደርጉ መተግበሪያዎችን በመለያዎ ቅንብሮች ውስጥ መተግበሪያዎች ትርን በመጎብኘት መዳረሻቸውን መሻር ይችላሉ።

ይህንን ጽሁፍ ያጋሩ